Fana: At a Speed of Life!

37ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ውድድር ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 17፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) 37ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ውድድር በዛሬው ዕለት ተካሄደ፡፡
 
የተካሄዱት የውድድሮች ርቀትም የ10ኪ.ሜ አዋቂ ሴቶች ፣ 6 ኪሎ ሜትር ወጣት ሴቶች ፣ የ8 ኪሜ የወጣት ወንዶች ፣ 10 ኪሎ ሜትር ወንዶች ፣ ድብልቅ ሪሌ እና ቬትራን ናቸው፡፡
 
በዚህም በ10ኪሎ ሜትር አዋቂ ሴቶች አትሌት ፅጌ ገ/ሰላማ ከትግራይ ፖሊስ አንደኛ ፣ ፎቴን ተስፋይ ከመሶቦ እና ሹሬ ደምሴ ከኦሮሚያ ፖሊስ 2ኛ እና 3ኛ በመሆን አጠናቀዋል፡፡
 
በቡድን ደግሞ አማራ ክልል አንደኛ ደረጃን በመያዝ ሲያጠናቅቅ መሰቦ ሁለተኛ እና ኦሮሚያ ፓሊስ ሶስተኛ ደረጃን ይዘው ማጠናቀቅ ችለዋል፡፡
 
በ6 ኪሎ ሜትር ወጣት ሴቶች በበቀለች ተክሉ ከኦሮሚያ ክልል በአንደኝነት ያጠናቀቀች ሲሆን መላክናት ውዱ ከአማራ ክልልና አሚናት አህመድ ከሃዋሳ ከነማ ሁለተኛና ሶስተኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቀዋል።
 
በዚህ ውድድር በቡድን አማራ ክልል ፣ ኦሮሚያ ክልል እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ ማጠናቀቃቸው ተጠቁሟል፡፡
 
በ8 ኪሎ ሜትር ወጣት ወንዶች በተካሄደው ውድድር በረሁ አረጋዊ ከሱር ኮንስትራክሽን አንደኛ ደረጃን በመያዝ ያጠናቀቀ ሲሆን በረከት ዘለቀ እና አዲሱ ይሁኔ ከአማራ ክልል ሁለተኛ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቅ ችለዋል፡፡
 
በቡድን በተካሄደው የ8 ኪሎ ሜትር ወጣት ወዶች አማራ ክልል ፣ ኦሮሚያ ክልል እንዲሁም ጉና ንግድ ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡
 
በ10 ኪሎ ሜትር አዋቂ ወንዶች ንብረት መላክ እና አስረሴ ጌታሁን ከአማራ ክልል አንደኛ እና ሁለተኛ በመሆን ሲያጠናቅቁ ዲዳ ለማ ከአሮሚያ ክልል ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ነው ያጠናቀቀው፡፡
 
አማራ ክልል ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና መከላከያ የቡድን ውድድሩን ከአንድ እስከ ሶስት በመያዝ አጠናቀዋል፡፡
በተመሳሳይ ድብልቅ ሪሌ በቡድን ኦሮሚያ ክልል ፣ ኦሮሚያ ውሃ ስራዎች እና አዳማ ከተማ ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ወጥተዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.