Fana: At a Speed of Life!

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት የምስረታና የመክፈቻ ጉባኤ ነገ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ መሰከረም 23፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የኢፌዲሪ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት የምስረታና የመክፈቻ ጉባኤ ነገ መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ እንደሚካሄድ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታወቀ፡፡

የምክር ቤቱ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ በሁለቱ ምክር ቤቶች የመክፈቻ ጉባኤ ላይም ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር የሚያደርጉ ሲሆን÷ የጉባኤው ሂደትም በቀጥታ ስርጭት የሚተላለፍ ይሆናል ተብሏል፡፡

በጉባኤውም በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ አገራት አምባሳደሮችና የአለም አቀፍ ተቋማት ሃላፊዎች፣ የሐይማኖት አባቶች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በመስራች ጉባኤው ላይ ይገኛሉ ፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.