በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ 1ሺህ 127 ዜጎች ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ፣ሰኔ 24፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በተከናወነ ዜጎችን ከሳዑዲ ዓረቢያ የመመለስ ሥራ 1 ሺህ 127 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማዕከላት እንዲሄዱ መደረጉ ተገልጿል፡፡
እስካሁን ድረስ በተከናወነው ዜጎችን ወደ ሀገራቸው የመመለ ሥራ÷ 45 ሺህ 325 ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!