Fana: At a Speed of Life!

ሴኔጋላዊው ሳዲዮ ማኔ የካፍ የዓመቱ ምርጥ አፍሪካዊ እግር ኳስ ተጫዋች ሆኖ ተመረጠ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የቀድሞው የሊቨርፑል ኮከብ እና የአሁኑ የባየር ሙኒክ አዲስ ፈራሚ ሳዲዮ ማኔ የካፍ የዓመቱ ምርጥ አፍሪካዊ ተጫዋች ሆኖ ተመርጧል፡፡
ሳዲዮ ማኔ በክለቡ ሊቨርፑል ማራኪ የውድድር ዓመት ከማሳለፉ በተጨማሪ÷ ሀገሩ ሴኔጋል የአፍሪካ ዋንጫ ሻምፒዮን እንድትሆን ከፍተኛ አስተዋፅኦ በማድረጉ ነው የካፍ የ2022 ምርጥ ተጫዋች በመሆን የተመረጠው፡፡
በሞሮኮ ራባት በተካሄደው ምርጫ÷ ከሳዲዮ ማኔ በተጨማሪ የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ አሊዮ ሲሴ የዓመቱ ምርጥ አሰልጣኝ ሽልማትን አሸንፏል፡፡
የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን የዓመቱ ምርጥ ብሔራዊ ቡድን ሽልማትን፣ ዋይዳድ ካዛብላንካ የዓመቱ ምርጥ አፍሪካዊ እግር ኳስ ቡድን ሽልማትን እንዲሁም ማሜሎዲ ሰንዳውንስ የዓመቱ ምርጥ የሴቶች እግር ኳስ ክለብ ሽልማትን አሸንፈዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.