Fana: At a Speed of Life!

አቡበከር ናስር የማሜሎዲ ሰንዳውንስ ዝውውሩን አጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና እና የዋሊያዎቹ አጥቂ አቡበከር ናስር የማሜሎዲ ሰንዳውንስ ዝውውሩን ማጠናቀቁ ተገልጿል፡፡
 
አቡበከር ከወራት በፊት ከማሜሎዲ ሰንዳውንስ ጋር በደረሰው ስምምነት መሰረት ወደ ደቡብ አፍሪካ ቢያቀናም ዝውውሩ በፊፋ ሳይረጋገጥ ቆይቷል፡፡
 
ይሁን እንጂ አጥቂው በዛሬው ዕለት ወደ ደቡብ አፍሪካው ክለብ ማሜሎዲ ሰንዳውንስ የሚያደርገውን ዝውውር ማጠናቀቁን የሚገልፅ የፊፋ አይ ቲ ሲ (ITC) ማረጋገጫ አግኝቷል።
 
ይህን ተከትሎም ከዛሬ ጀምሮ በቋሚ ውል የማሜሎዲ ሰንዳውንስ ተጫዋች እንደሆነ መረጋገጡን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.