Fana: At a Speed of Life!

የአሜሪካ ፣ ጃፓን እና ደቡብ ኮሪያ ባሕር ኃይሎች ጥምር ወታደራዊ ልምምድ ሊያካሂዱ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰሜን ኮሪያ በቅርቡ ያደረገችውን የሚሳኤል ሙከራ ተከትሎ የአሜሪካ፣ ጃፓን እና ደቡብ ኮሪያ ባሕር ኃይሎች በጥምረት በጃፓን ባሕር ላይ የፀረ-ሰርጓጅ መርከብ ጥቃት ልምምድ ሊያካሂዱ መሆኑ ተገለጸ።

ሀገራቱ ከ2017 ወዲህ የአሜሪካውን በኒውክሌር ኃይል የሚንቀሳቀስ የአውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ ያካተተ ጥምር ልምምድ ሲያደርጉ የመጀመሪያው እንደሚሆንም ተመላክቷል፡፡

ነገ የሚጀምረው ጥምር ልምምድ ከፈረንጆቹ 2017 በፊት በደቡብ ኮሪያ፣ አሜሪካ እና ጃፓን መካከል የተገባውን የወታደራዊ ትብብር ስምምነት ወደ ቀደመ ቦታው ለመመለስ ያለመ ነውም ተብሏል፡፡

ውጥረቱ የተባባሰው የአሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት ካማላ ሃሪስ በእስያ የጉብኝት መርሐ-ግብራቸው መሠረት የደቡብ ኮሪያውን ፕሬዚዳንት ዩን ሱክ-ዮል ጋር ተገናኝተው ከተወያዩ በኋላ መሆኑ ተነግሯል፡፡

የሁለቱን ወገኖች ግንኙነት ተከትሎም የአሜሪካው ነጩ ቤተ- መንግስት ሀገራቱ ጃፓንን ጨምረው በቀጣይ በሚኖራቸው የሦስትዮሽ የደኅንነት ትብብሮች እና ለሚሰነዘሩባቸው ጥቃቶች በጋራ በሚሰጧቸው ምላሾች ላይ መወያየታቸውን ጠቁሟል፡፡

ባሳለፍነው ሰኞ በተካሄደው የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ሰሜን ኮሪያ የሀገራቱ ልምምድ ለደኅንነቴ ያሰጋኛል ስትል መግለጿን አር ቲ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.