Fana: At a Speed of Life!

በኬንያ የኪጃቤ ግድብ መደርመስ ባስከተለው የጎርፍ አደጋ ከ45 በላይ ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በምዕራብ ኬንያ በጣለው ተከታታይ ከባድ ዝናብ አሮጌው የኪጃቤ የውኃ ግድብ መደርመስ ባስከተለው የጎርፍ አደጋ በካሙቹሪ መንደር የ45 ሰዎችን ሕይወት ቀጠፈ፡፡

የሀገሪቱ ባለስልጣናት እንዳሉት፤ አደጋው ያጋጠመው በአካባቢው የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ ነው፡፡

የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋው በመኖሪያ ቤቶች እና የመንገድ መሠረተ-ልማቶች ላይም ጉዳት ማድረሱን ጠቅሶ የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡

አሁንም የነፍስ አድን ሥራው ተጠናክሮ መቀጠሉን የጠቀሰው ዘገባው÷ የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችልም አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.