Fana: At a Speed of Life!

አርጀንቲና የዓለም ዋንጫ ቆይታዋን የሚወስነውን ወሳኝ ጨዋታ ምሽት ታደርጋለች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኳታሩ ዓለም ዋንጫ ዛሬ የምድብ ሦስት እና አራት የመጨረሻ ጨዋታዎች ይካሄዳሉ፡፡

በምድብ አራት ቱኒዚያ ከፈረንሳይ እንዲሁም አውስትራሊያ ከዴንማርክ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

በምድብ አራት ፈረንሳይ ስድስት ነጥብ በመያዝ ከምድቡ ወደ ቀጣይ ዙር ማለፏን አስቀድማ ስታረጋግጥ አውስትራሊያ ሦስት ቱኒዚያ እና ዴንማርክ ደግሞ በ1 ነጥብ ይዘው የምሽቱን ጨዋታ ያካሂዳሉ።

በተመሳሳይ ከምድብ ሦስት ሳዑዲ አረቢያ ከሜክሲኮ እና ፖላንድ ከአርጀንቲና ምሽት አራት ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

ምድብ ሶስትን ፖላንድ በአራት ነጥብ ስትመራ አርጀንቲና እና ሳዑዲ አረቢያ ሦስት ሦስት ነጥብ በመያዝ ይከተላሉ፡፡

ሜክሲኮ በአንድ ነጥብ የምድቡን የመጨረሻ ደረጃ ይዛለች።

በምሽቱ ጨዋታ ፖላንድ ጥሎ ማለፉን ለመቀላቀል ማሸነፍ ወይም አቻ መለያየት በቂዋ ይሆናል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.