Fana: At a Speed of Life!

የቀድሞው የዩጎዝላቪያ ተጫዋች ሲንሳ ሚሃይሎቪች ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣሥ 7 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የኢንተር ሚላን እና ላዚዮ ተከላካይ ሲንሳ ሚሃይሎቪች ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

ሚሃይሎቪች በዛሬው እለት በጣሊያን ሮም ህይወቱ ማለፉን ደይሊ ሜይል አስነብቧል።

በድንቅ ቅጣት ምት ጎሎቹ የሚታወቀው የቀድሞዋ ዩጎዝላቪያ ጠንካራ ቡድን አባል የነበረው ሚሃይሎቪች በ53 አመቱ ነው ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው።

ሚሃይሎቪች በጣሊያኖቹ ኢንተር ሚላን፣ ሳምፕዶሪያ፣ ሮማ እና ላዚዮ ክለቦች በተከላካይነት እና በአማካይነት በመጫወት አሳልፏል።

በተለይም ከላዚዮ ጋር ስኬታማ ጊዜያትን ያሳለፈ ሲሆን፥ በኢንተር እና ላዚዮ ቆይታው 2 የጣሊያን ሴሪ አ ዋንጫዎችን ጨምሮ የጣሊያን ዋንጫን አሸንፏል።

ከዚህ ባለፈም ከውድድር የታገደውንና ላዚዮ የመጨረሻው ክለብ በመሆን ያሸነፈውን የአውሮፓ የአሸናፊዎች ዋንጫን ማንሳት ችሏል።

በብሄራዊ ቡድን ደረጃ ከዩጎዝላቪያ ጋር በ1998ቱ የዓለም ዋንጫ እና ኔዘርላንድስ እና ቤልጂየም ባስተናገዱት የዩሮ 2000 ተሳትፏል።

በብሄራዊ ቡድን ደረጃ 63 ጊዜ በመጫወት 10 ጎሎችን በስሙ አስመዝግቧል።

ዘወትር በሚታወስበት ድንቅ ቅጣት ምቶቹም 28 ጎሎችን ከመረብ አሳርፏል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.