Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ ባህርዳር ከተማ ኢትዮ ኤሌክትሪክን 3 ለ 1 አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ባህርዳር ከተማ ኢትዮ ኤሌክትሪክን 3 ለ 1 አሸነፈ፡፡

በድሬዳዋ ስታዲየም በተካሄደው የ16ኛ ሳምንት መርሐ ግብር የጣና ሞገዶቹ ከመመራት ተነስተው በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች በተከታታይ ባስቆጠሯቸው ጎሎች ሶስት ነጥብ አስመዝግበዋል፡፡

ለባህር ዳር ከተማ ሀብታሙ ታደሰ ሁለት ጎሎችን ሲያስቆጥር ፉአድ ፈረጃ ቀሪዋን አንድ ጎል አስቆጥሯል፡፡

የኢትዮ ኤሌክትሪክን ብቸኛ ጎል አብነት ደምሴ በ51ኛው ደቂቃ አስቆጥሯል፡፡

ውጤቱን ተከትሎም የጣና ሞገዶቹ ነጥባቸውን ወደ 30 ከፍ በማድረግ ከኢትዮጵያ መድን ጋር እኩል ሁለተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችለዋል፡፡

እንዲሁም ምሽት 1 ሰዓት ላይ በተካሄደው የ16ኛ ሳምንት መርሐግብር ጨዋታ አዳማ ከተማ ፋሲል ከነማን 2 ለ1 አሸንፏል፡፡

በሚኪያስ አየለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.