ከንቲባ አዳነች በአርቲስት ዘሪሁን ወዳጆ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ
አዲስ አበባ፣ ሚዝያ 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአርቲስት ዘሪሁን ወዳጆ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ፡፡
አርቲስት ዘሪሁን ወዳጆ የኦሮሞን ሕዝብ ብሶት፣ ድል፣ ተስፋ እና ደስታ በውብ ጥበብ ሲያጎላ የኖረ መሆኑን ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡
በኦሮሞ ሕዝብ ታሪክ ውስጥ ጉልህ ስፍራ ያለው አርቲስት እንደነበርም ጠቁመዋል፡፡
ከንቲባ አዳነች ለቤተሰቦቹ እና ለአድናቂዎቹ መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!