Fana: At a Speed of Life!

የትንሳኤ በዓልን ስናከብር ለሰዎች ሰላም በመጸለይ ይሁን- ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የትንሳኤ በዓልን ስናከብር ለሰው ልጆች ሰላምና ደኅንነት በመጸለይና የተቸገሩ ወገኖችን በማገዝ ሊሆን ይገባል ሲሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ገለጹ፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ-ክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የትንሳኤ በዓልን በማስመልከት ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞት መልዕክት÷ በዓለ ትንሳኤ የእግዚአብሔር ፍቅር መገለጫና የተስፋችን ማሳያ መሆኑን ልንገነዘብ ይገባል ብለዋል።

በዓሉን ስናከብርም ለእግዚአብሔር ክብርና ለሰው ልጆች ደኀንነት በአንድነት በመቆም መሆን አለበት ሲሉ አስገንዝበዋል።

በፍቅር በመተሳሰብና በመተጋገዝ እንዲሁም የተቸገሩ ወገኖችን በመደገፍ ማክበር እንደሚገባም ነው የመከሩት፡፡

ለሰው ልጆች ሁሉ ሰላምና ደኅንነት በመጸለይና የተቸገሩ ወገኖችን በማገዝ ሊሆን እንደሚገባ ለምዕመኑ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የኢየሱስ ክርስቶስን ትንሳኤ ስናከብር የኛንም ትንሳኤ በማሰብ ሊሆን ይገባል ሲሉም ነው ያስገነዘቡት ብጹዕነታቸው፡፡

እግዚአብሔር ክህደትን፣ ጥላቻን፣ መለያየትን፣ ራስን ብቻ መውደድን ጨምሮ ጸያፍ ተግባራትን የተጸየፈ ምዕመንን ማየት ይፈልጋል ሲሉም አስረድተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.