Fana: At a Speed of Life!

ዓለም አቀፉ የምርጫ ታዛቢ ትራምፕ ምርጫው ተጭበርብሯል ማለታቸው ዴሞክራሲን የሚሸረሽር ነው አለ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2013 (ኤፍቢሲ) አሸናፊው እስካሁን ባልታወቀበት የአሜሪካ ምርጫ ዓለም አቀፉ የምርጫ ታዛቢ ቡድን ዶናልድ ትራምፕ ምርጫው ተጭበርብሯል በሚል ያቀረቡትን አቤቱታ ተቸ፡፡
 
ታዛቢ ቡድኑ ምርጫው መጭበርበሩን የሚያሳይ ምንም ማስረጃ የለም ብሏል፡፡
 
የ2020 ምርጫ ጠንካራ ፉክክር የታየበትና በአግባቡ የተካሄደ መሆኑንም ነው የገለጸው፡፡
 
ቡድኑን የሚመሩት ማይክል ጆርጅ ሊንክ አንድ በስልጣን ላይ የሚገኝ መሪ መሰረት የሌለው ውንጀላ ማቅረቡ ህዝብ በዴሞክራሲ ተቋማት ላይ ያለውን አመኔታ እንዲያጣ ያደርጋል ብለዋል፡፡
 
ታዛቢ ቡድኑ ከ39 ሃገራት የተውጣጡ 102 ሰዎችን የያዘ ነው ተብሏል፡፡
 
በተጨማሪም በሃገሪቱ የሚገኙ መገናኛ ብዙሃን አካሄድም እንዳሳሰበው ነው የገለጸው፡፡
 
በአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በጠባብ ልዩነት የዴሞክራቱ እጩ ጆ ባይደን በመምራት ላይ ይገኛሉ፡፡
 
አሸናፊውን ፕሬዚዳንት ለማወቅ አሜሪካን ጨምሮ በመላው ዓለም ከትናንት ጀምሮ በጉጉት እየተጠበቀ ሲሆን ምናልባት አመሻሽ ካልሆነም እስከነገ ማለዳ ሊታወቅ ይችላል ተብሏል፡፡
 
ምንጭ፡-አልጀዚራ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.