ዶክተር አብረሃም በላይ ከዓለም ባንክ የፕሮጀክት ንድፍ ቡድን ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር አብረሀም በላይ ከዓለም ባንክ የፕሮጀክት ንድፍ ቡድን ጋር ተወያዩ።
ውይይቱ በኢትዮጵያ በዲጂታል የንግድ ሥራ ፈጠራ እና ለፈጠራ ሀሳቦች የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ በተጀመሩ ስራዎች ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል።
ሚኒስትሩ ቡድኑ በዘርፉ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ እንዲያፋጥን መጠየቃቸውን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision