Fana: At a Speed of Life!

የኢንዱስትሪ ፖርኮች ልማት ኮፖሬሽን ለአፋር ክልል ተፈናቃዮች የ15 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳሰ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪ ፖርኮች ልማት ኮፖሬሽን በአፋር ክልል ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች 15 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የአይነት ድጋፍ አድርጓል፡፡
 
ድጋፉን የኢንዱስትሪ ፖርኮች ልማት ኮፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሳንዶካን ደበበ ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ አስረክበዋል፡፡
 
አቶ ሳንዶካን በርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ እንደተናገሩት÷የሽብር ቡድኑ ህወሓት በአፋር ክልል ሊያሳከው ያለመው ጥፋት በህዝቡ ጀግንነት ተቀልብሷል።
 
ለተወሰኑ ጊዜያት በገባባቸው ቦታዎችን በሰዎች እና በንብረት ላይ ያስከተለው ውድመት ከፍተኛ መሆኑንም አንስተዋል፡፡
 
በሽብር ቡድኑ ወራራ ሳቢያ ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚሆን የ15 ሚሊየን ብር የቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉን ዋና ስራ አስፈጻሚው ገልጸዋል፡፡
 
የተደረገው ድጋፍ አልሚ ምግብ፣ አልባሳት፣ የሴቶ የንጽህና መጠበቂያ እና የማብሰያ ቁሳቁስ ያካተተ መሆኑ ተገልጿል፡፡
 
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበው÷በሽብር ቡድኑ ህወሓት ሃገር በደፈረትበት ወቅት ንብረት ከመዝረፍ ባለፈ በሰዎች ላይም አሰቃቂ ግድያ መፈጸሙን አንስተዋል፡፡
 
በበላይ ተስፈዬ
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.