Fana: At a Speed of Life!

ቀጣይ ግባችን ዘላቂ ሰላምን በማረጋገጥ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ልማትና እድገት ማረጋገጥ ሊሆን ይገባል- የሃይማኖት አባቶች

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቀጣይ ግባችን ዘላቂ ሰላምን በማረጋገጥ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ልማትና እድገት ማረጋገጥ ሊሆን ይገባል ሲሉ የተለያዩ ሃይማኖት አባቶች ገለጹ፡፡
 
በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከተለያዩ የሃይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች እና ታዋቂ ግለሰቦች ጋር ውይይት አካሂዷል።
 
የውይይቱ ተሳታፊዎችኢትዮጵያን ከትውልድ ትውልድ በተላለፉ ልዩነቶች ምክንያት የተፈጠሩ መቃቃሮችን ማስወገድ ፤ ከዘመናት የግጭት አዙሪት ውስጥ በመውጣት ዘላቂ ሰላም ማረጋጋጥ ይገባል ብለዋል፡፡
 
እንደ አገር ገለልተኛ ተቋም በማቋቋም እና ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ያካተተ ብሔራዊ ውይይት ለማድረግ እየተሰሩ ያሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች የሚበረታቱ እንደሆኑም ነው የተናገሩት ፡፡
 
እንደ ከተማ ብሎም እንደ አገር ቀጣይ ግባችን ተገደን የገባንበትን ጦርነት በድል በመደምደም ሙሉ ትኩረታችንን በሁለንተናዊ የአገር ልማትና እድገት ላይ ሊሆን ይገባል ነው ያሉት ።
 
በቀጣይም በወራሪው ቡድን ምክንያት ለችግር የተጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎችን ከማቋቋም ጎን ለጎን የወደሙ የተለያዩ የትምህርት እና የጤና ተቋማትን ለመገንባት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱም ቃል ገብተዋል ።
 
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲንባ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው ÷ ተገደን የገባንበትን ጦርነት በተባበረ ክንድ በድል በማጠናቀቅ በጦርነቱ ተጎጂ የሆኑ አካለትን መልሶ የማቋቋም ስራ ማከናዋን አለብን ብለዋል፡፡
 
የታየውን ከፍተኛ ህብረ ብሔራዊ አንድነትና መነሳሳት አሟጦ በመጠቀም በሁለንተናዊ የአገር ልማትና እድገት ላይ ትኩረት በማድረግ እየተሰራ እንደሆነ መግለጻቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.