Fana: At a Speed of Life!

ማዕድን ከሚወጣባቸው በርካታ ሀገራት ኢትዮጵያን የተረጋጋች እና ሠላማዊ ሆና አግኝቻታለሁ – ጆርገን ኤቭጄን

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኖርዌዩ አኮቦ ሚኔራልስ ኩባንያ በኢትዮጵያ ሰገሌ የወርቅ ማዕድን ቦታ ወርቅ እና አብረው የሚገኙ ማዕድናትን ለማውጣት የሚያስችለውን ፈቃድ አግኝቶ ሥራ መጀመሩን አስታወቀ፡፡

የአኮቦ ሚኔራልስ ኩባንያ ኃላፊ ጆርገን ኤቭጄን÷ኩባንያቸው በኢትዮጵያ መዋዕለ ነዋይ ለማፍሰስ ሲወስን እንዴት ግጭት በተቀሰቀሰበት የጦር ቀጠና ትሄዳላችሁ የሚሉ ጥያቄዎች ከሌሎች አቻ ኩባንያዎች ሲቀርብላቸው እንደነበር ተናግረዋል፡፡

ከኩባንያዎቹ የማስጠንቀቂያ አስተያየቶች በተጨማሪ አዲስ አበባ በአሸባሪው እጅ ወድቃለች የሚል የተጋነነ መረጃ ሲደርሰን ነበርም ብለዋል፡፡

መረጃው ፍጹም ሃሰት እንደሆነና እንዲያውም ኢትዮጵያ ከሌሎች የማዕድን ማውጣት ሥራ ከሚካሄድባቸው በርካታ ሀገራት ይልቅ የተረጋጋች እና ሠላማዊ ሀገር እንደሆነች መስክረዋል፡፡

ህወሓት ሀገሪቷን ከወረረበት ጊዜ ጀምሮ የተቀናጁ የመገናኛ ብዙኃን የሃሰት ዘገባዎች ሲሰሩ እንደነበር አስታውሰው ዘገባውን ተከትሎ በአዲስ አበባ የሚገኘው የኖርዌይ ኤምባሲ የኖርዌይ ዜጎች አዲስ አበባን ለቀው እንዲወጡ ጥሪ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡

ኤምባሲው ጥሪ ካደረገበት ቀን በፊትም ሆነ በኋላ እርሳቸውም ሆኑ ሠራተኞቻቸው ምንም የሽብርም ሆነ ያለመረጋጋት እንቅስቃሴ በመዲናዋ እንዳላስተዋሉና ሥራቸውን እየሰሩ እንደሆነም ነው የገለጹት፡፡

ማዕድን የሚያወጡበት ቦታ በአሸባሪው ተይዞ ከነበረው አካባቢ 1 ሺህ 500 ኪሎ ሜትር እንደሚርቅ እና አሁን ላይ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ የትግራዩን ወራሪ ቡድን ለመቅበር እየተቃረበ እንደሆነ አረጋግጠናል ብለዋል ጆርገን ኤቭጄን፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.