Fana: At a Speed of Life!

የቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከበር አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጓል – ፖሊስ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ከሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ ከፌዴራል ፖሊስ፣ ከኦሮሚያ ፖሊስ፣ ከድሬዳዋ ፖሊስ እና ከሐረሪ ፖሊስ በተውጣጣ በዕዝ የሚመራ ግብረ ኃይል በቂ ዝግጅት ማድረጉ ተገልጿል፡፡
 
የቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሐረርጌ ዞን ቁልቢ ከተማ በየዓመቱ ታህሳስ 19 ቀን በደማቅ ሁኔታ የሚከበር በዓል ነው፡፡
 
በዓሉ ያለምንም የጸጥታ ችግር በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ከሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ፣ ከኦሮሚያ ፖሊስ፣ ከድሬዳዋ ፖሊስ እና ከሐረሪ ፖሊስ የተውጣጣ በዕዝ የሚመራ ግብረ ኃይል ከአካባቢው አስተዳደር አካለት ጋር ጥምረት በመፍጠር በቂ ዝግጅት ማድረጉን የፌደራል ፖሊስ አስታውቋል፡፡
 
ጥምር የጸጥታ አካላቱ የቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ንግስ ክብረ በዓል በሰላም ተከብሮ እንዳይጠናቀቅ ከአንዳንድ ምዕራብውያን ሀገራት የተሰጣቸውን ተልዕኮ ለማስፈጸም የሚንቀሳቀሱት አሸባሪው ህወሓት እና ተላላኪው ሸኔ የበዓሉ ደማቅ ድባብና ገጽታ ለማበላሸት ሌት ተቀን እየሰሩ መሆናቸው ተመላክቷል፡፡
 
አሸባሪዎቹ ህዝበ ክርስቲያኑ ላይ ጥቃት እንዳያደርሱ በተናበበ እና በተቀናጀ መልኩ በጋራ በመስራት የጥፋት ተልዕኳቸው እንዳይሳካ በዕዝ የሚመራው ጥምር የጸጥታ ኃይሉ በቂ ዝግጅት አድርጎ ከወዲሁ በተቀናጀ ሁኔታ መንቀሳቀስ መጀመሩ ነው የተገለጸው፡፡
 
ጥምር የጸጥታ ኃይሉ ወቅቱን የሚመጥን ልዩ የፀጥታ የጋራ እቅድ በማዘጋጀት ታህሳስ 10 ቀን 2014 ዓ.ም የውይይት መድረክ በመፍጠር በዕቅዱ ዙሪያ መምከሩን ከፌዴራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ከውይይቱ በኋላም ተጋላጭና ልዩ ትኩረት የሚፈልጉ አካባቢዎችን በመለያት ህዝበ ክርስቲያኑ በዓሉን ያለምንም የፀጥታ ችግር በድምቀት እንዲያከብር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ በዕቅዱ መሰረት ወደ ተግባር ለመግባት ስምምነት ላይ መድረሱ ተገልጿል፡፡
 
የአካባቢው ህብረተሰብም ለእንግዶች ቅድሚያ በመስጠት የተለመደውን ትብብር እንዲያደርግላቸው እና የተለየ ሁኔታም ሲያጋጥም በአካባቢው ለሚገኙ የጸጥታ ኃይሎች በፍጥነት ጥቆማ እንዲሰጥ እንዲሁም አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.