Fana: At a Speed of Life!

አልማ እና ግሎባል አሊያንስ ለኢትዮጵያውያን መብቶች ድርጅት በአፋር ክልል ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል አሸባሪው ህወሓት በፈፀመው ጥቃት ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚውል የአማራ ልማት ማህበርና ግሎባል አሊያንስ ለኢትዮጵያውያን መብቶች ድርጅት የ10 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረጉ፡፡
የአማራ ልማት ማህበርን ድጋፍ የማህበሩ ዋና ስራ አስፈፃሚ መላኩ ፈንታየ5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አስረክበዋል።
የሰብአዊ መብት ተሟጋችና የግሎባል አሊያንስ ለኢትዮጵያውያን መብቶች ድርጅትን ድጋፍ ደግሞ ታማኝ በየነ የ5 ሚሊየን ብር ግምት ያላቸው በአይነት የተለያዩ ምግብ ነክ ቁሳቁስ አስረክበዋል፡፡
አቶ መላኩ ፈንታ እንደተናገሩት ያለንን ወገናዊነት እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር ለመግለፅ ሲባል የአማራ ልማት ማህበር የ5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን ከክልሉ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የሰብአዊ መብት ተሟጋችና የግሎባል አሊያንስ ለኢትዮጵያውያን መብቶች ድርጅት ሊቀ መንበር ታማኝ በየነ እንደገለጹት÷ እስካሁን ድረስ አፋር ተበደልኩ ብሎ ምንም ሳይደረግለት ማንነቱን በመንገድ ጥራት፣ በህንፃ ብዛት እና በፋብሪካ ሳይለካ ለኢትዮጵያ ደሙን በማፍሰስ፣ አጥንቱን በመከስከስ ኢትዮጵያን ያቆየ ጀግና ህዝብ ነው፡፡
ድጋፉን የተረከቡት የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በበኩላቸው÷ አሸባሪው ህወሓት ያሰበው ሀገር የማፍረስ ተግባሩ ባይሳካም÷ የማይሽር ጠባሳ በህዝባችን ላይ ፈፅሟል ነው ያሉት።
የችግራችን ተካፋይ በመሆናችሁና ላደረጋችሁልን ድጋፍ በአፋር ህዝብ እና መንግስት ስም እናመሰግናለን ብለዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.