Fana: At a Speed of Life!

ምእራባውያኑ ስለ ኢትዮጵያ የያዙት የተዛባ ፖሊሲ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሸባሪው የህወሓት ቡድን የቀድሞ ባለሥልጣናት ወደ ጦርነት የገቡት የሥልጣን ጥማቸው ስላልቆረጠላቸው እና በሥልጣን ዘመናቸው ከሠሯቸው የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ክስ ማምለጥ እንደማይችሉ ስለተረዱ መሆኑን የቀድሞው የኦሮሚያ ምክትል ጠቅላይ አቃቤ ህግ እና የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ናጌሳ ዱቤ አመላከተ፡፡

ነዋሪነቱ በሚኒአፖሊስ ሚኔሶታ ያደረገው የሰብዓዊ መብት ተከራካሪና የቀድሞ የኦሮሚያ ምክትል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ናጌሳ ዱቤ፥ አሸባሪ ቡድኑ ሥልጣን ላይ ለ27 ዓመታት በነበረበት ጊዜ በፖለቲካ አመለካከቱ ዘብ ጥያ እንዳወረደውና ስቃይ እንዳደረሰበት አስፍሯል፡፡

ናጌሳ ዱቤ፥ “ዘ አፍሪካ ሪፖርት ላይ እንደጻፈው” አሁን አሜሪካ ለአሸባሪው የህወሓት ቡድን የምታደርገው ድጋፍ እርሱን ጨምሮ በርካታ ኢትዮጵያውያንን ግራ እያጋባ እንደሚገኝ ጠቁሟል፡፡

ይባስ ብሎ በአሸባሪ ቡድኑ በተቀሰቀሰው ጦርነት የተሳቡት የአሜሪካ ዲፕሎማቶች እና ጋዜጠኞች አሜሪካ ለአሸባሪ ቡድኑ የምታደርገው ምንም አይነት ድጋፍም ሆነ አድልኦ የለም ብለው ይከራከራሉ፡፡

እንዲያውም አሜሪካ ከምንም በላይ ለኢትዮጵያውያን ሕይወት እንደምትጨነቅ፣ የሀገሪቷ ወቅታዊ ሁኔታም እንዳሳሰባት እና ሠላማዊ መፍትሄ እንዲፈለግ እንደምትሻ እየወተወተች ይገኛል፡፡

ኢትዮጵያዊያን ደግሞ ዲፕሎማሲው ለአሸባሪው የህወሓት ቡድን ያደላ እና በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነት ለተፈረጀው አማፂ እውቅና የሰጠ ነው ብለው እንደሚያምኑም አመላክቷል፡፡

ለአሸባሪው የህወሓት ቡድን ከመንግስት እኩል እውቅና መስጠትና በአንድ ጠረጴዛ እንዲደራደሩ መጋበዝ የኢትዮጵያን መንግስት መናቅ ነውም ሲሉ ይከራከራሉ ብሏል፡፡

የሰብዓዊ መብት ተከራካሪው፥ የአሜሪካ አቀራረብ ኢትዮጵያውያንን ግራ ያጋባ እና አንዳንድ ዓለም አቀፍ አጋሮቻቸውንም ጭምር በጥርጣሬ እንዲመለከቱ ያደረገ እንደሆነ ትዝብቱን ጽፏል፡፡

እንደነዚህ ያሉ ጦርነቱ ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ የውጪ ጣልቃ ገብነቶች የሚከሰቱት ውጊያው በትክክል ለምን እንደሚካሄድ እና ውጤቱን ካለመረዳት የሚመነጭ ነው ሲልም ያስረዳል፡፡

ትክክለኛ የግጭቱን ወይም የጦርነቱን ምክንያቶች ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሳይታክቱ ማስረዳት የውጪ ኃይሎች በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ እንዳይገቡ እና ትክክለኛውን መረጃ ይዘው መፍትሄ እንዲሰጡ ያስችላቸዋልም ሲል ገልጿል፡፡

እውነት ለመናገር ይላል ጸሃፊው፥ የቀድሞ የትግራይ አማጺ ባለሥልጣናትን ወደ አመጽ የመራቸው የብልጽግና ውህድ ፓርቲ በክልላቸው እውን እንዲያደርጉ እና እንደ ሀገር እንዲቀላቀሉ መጠየቃቸው አይደለም፤ የፌዴራሉ መንግስት ተቀባይነት የለውም ብሎ የሰረዘው በክልላቸው ያካሄዱት “የጨረባ” ምርጫም አይደለም፤ የቀድሞው የህወሓት አምባሳደር ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ እንደሚለው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሥልጣን ጥም ስላለው ሁሉንም ኃላፊነት ለመሰብሰብ ይፈልጋል የሚለው ስጋትም በባለሥልጣናቱ ዘንድ የለም፡፡

የአሸባሪው የህወሃት ቡድን አመጽ እና ወደ ጫካ መግባት ትክክለኛ ምክንያት ፣ በመጀመሪያ ደረጃ የባለሥልጣናቱ የማያቋርጥ የሥልጣን ጥም እና ሀገሪቷን እንደገና በማስተዳደር በሙስና እና በመመዝበር የሚያገኙት የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ሲሆን በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ በ27 ዓመታት የሥልጣን ላይ ቆይታቸው ከሠሯቸው የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ተጠያቂነት ማምለጥ የሚችሉት ሥልጣን ላይ ሲቆዩ ብቻ እንደሆነ መስማማት ላይ በመድረሳቸው ነው ብሏል፡፡

ጥያቄው ይሄን እውነት ምን ያህሉ ተጽዕኖ ፈጣሪ የዓለም ፖለቲከኞች እና ሀገራት ያውቁታል የሚለው ነው … አስተያየቱን ለአንባቢዎቹ ዘ አፍሪካ ሪፖርት ላይ አጋርቷል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.