Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ህወሓት የአቅስታ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን የጦር ካምፕ በማድረግ ሲገለገልበት ቆይቷል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ወሎ ዞን ለጋንቦ ወረዳ የሚገኘው የአቀስታ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከ1945 ዓ.ም ጀምሮ ለአካባቢው ህጻናት እውቀትን እየመገበ ያሳደገውን ትምህርት ቤት በአሸባሪው ህወሓት ዝርፊያና ውድመት ደርሶበታል ሲል የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ገለጸ፡፡
የሽብር ቡድኑ በትምህርት ቤቱ በቆየበት አንድ ወር ጊዜ ውስጥ፥ የትምህርት ቤቱን ኮምፒውተሮች፣ የፕላዝማ ቴሌቪዥኖች፣ የቤተ ሙከራ እቃዎች፣ የትምህርት ቤቱን ውድ ንብረቶች የሚከማቹበትን ንብረት ክፍል፣ ጀኔሬተር፣ ሶላር፣ የኢንተርኔት መገልገያዎችን ጨምሮ ያሉ ንብረቶችን በሙሉ የቻለውን ዘርፏል ያልቻለውን ጥቅም በማይሰጥ መልኩ ማውደሙን ከክልሉ ትምህርት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የመምህራን የክብር መገለጫ የሆነው ጋወን ክብርን ዝቅ በሚያደርግ መልኩ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ቅርጫት ውስጥ ተጥሏል፤ ቢሮዎችና የመማሪያ ክፍሎችን እንደመጸዳጃ ክፍል ተጠቅመውበታል፡፡
በመማሪያ ክፍሎች ግድግዳ ላይ የሰውን ልጅ ስብእና የሚነኩ ጸያፍ ጽሁፎች ተጽፈዋል፡፡
ዛሬ ላይ ከ2 ሺህ 600 በላይ የሚሆኑ የአቀስታ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች እንደቀድሞው በቴክኖሎጅ የተደገፈ ትምህርት የሚማሩበት ኮምፒውተር ቀርቶ የሚቀመጡበት ወንበር እንኳን እንደሌላቸው ነው የተመላከተው፡፡
በመሆኑም የዚህ ትምህርት ቤት የቀድሞ ተማሪዎችና መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ድጋፍ እንዲያደርጉለት ተማሪዎችና መምህራን ጥሪ አቅርበዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.