Fana: At a Speed of Life!

ኢራን ሮኬት ወደ ህዋ አስወነጨፈች

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 21፣2014 (ኤፍ ቢሲ) ኢራን ሲሞርግ ወይም ፎኒክስ የተባለዉን ሮኬት ወደ ህዋ ማሰወንጨፏን አስታወቀች።

ኢራን በፈረንጆቹ 2015 የተደረሰውን የኒዩክሌር ስምምነት ዳግም ማነቃቃት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ንግግር እየተደረገ ባለበት በዚህ ወቅት ሮኬቱን ማስወንጨፏ ምናልባትም ምዕራባውያንን ለማበሳጨት ሊሆን እንደሚችል ግምት አለ።

ሃገሪቱ ያስወነጨፈችዉ ሮኬት ሶስት ሳተላይት የሚሸከሙ መሳሪያዎችን የያዘ ሲሆን፥ እስካሁን ሮኬቷ ምህዋሯ ላይ መድረስ አለመድረሷ የተገለፀ ነገር የለም፡፡

የኢራን መከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አህመድ ሆሴይኒ፥ ለሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን እንደተናገሩት፥ የሀገሪቱ የጠፈር ምርምር አካል የሆነችው ሮኬት በአንድ ጊዜ ሶስት ለጥናትና ምርምር የሚያስፈልጉ ቁሶችን መሸከም ችላለች።

ሀገሪቱ በቅርቡ ያስወነጨፈቻቸው ሮኬቶች ስኬት ቢያጣቸውም፥ የራሱን የጠፈር ምርምር በማድረግ ላይ ያለው የሀገሪቱ አብዮታዊ ዘብ ግን በዘርፉ ስኬታማ ሙከራዎችን እና ስራዎችን እያከናወነ መሆኑ ይነገራል።

ምንጭ ፡- ቲ አር ቲ

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.