Fana: At a Speed of Life!

በታይላንድ በ2024 ብቻ በከፍተኛ ሙቀት 61 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ተነገረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በታይላንድ የፈረንጆቹ 2024 ከገባ ጀምሮ በከፍተኛ ሙቀት ምክንያት 61 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በሀገሪቱ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ከፍተኛ ሙቀት መስተዋሉን ተከትሎ የጥንቃቄ መልዕክት ተላልፏል።

በመልዕክቱም በታይላንድ በተስተዋለው ከፍተኛ ሙቀት ሳቢያ 61 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ የተገለፀ ሲሆን በክስተቱ በ2023 ከሞቱት ሰዎች ቁጥር ጋር ሲነፃፀር በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩን አስታውቋል፡፡

የሀገሩቱ ሰሜናዊ ምስራቅ ክፍል አብዛኛውን የሟቾች ቁጥር ያስመዘገበ አካባቢ መሆኑ ነው የተገለፀው፡፡

በታይላንድ የዝናብ ወቅት መዘግየቱን ተከትሎ ከወትሮው በተለየ የተራዘመ ሞቃታማ የአየር ሁኔታ መስተዋሉ የተገለፀ ሲሆን በሀገሪቱ ከፍተኛ የተባለው 44 ነጥብ 2 ዲግሪ ሴልሺየስ የሙቀት መጠን ባለፈው ሚያዚያ ወር መመዝገቡ ተመላክቷል፡፡

በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ከፍተኛ የሙቀት መጠን የተመዘገበ ሲሆን የእስያ አህጉር ከአማካዩ ያለፈ ከፍተኛ የሙቀት መጠን እየተመታች እንደምትገኝ ዘ ስትሬት ታይምስ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.