Fana: At a Speed of Life!

እውቀት ከድንቁርና ቀንበር ነጻ የሚያወጣ መንገድ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) እውቀት ከድንቁርና ቀንበር ነጻ የሚያወጣ መንገድ እንደመሆኑ ዛሬ የተመረቀው አብርሆት ቤተ መፃህፍት ብዙ የተቆለፉብን መንገዶች መክፈቻ ቁልፍ እንደሆነ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለፁ።
 
ዛሬ አብርሆት ቤተ መፃህፍትን መርቀው የከፈቱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ በድንቁርና ምክንያት ሀገራቸውን የሚወጉና ለጠላቶች ተላላኪ የሆኑ እንዳሉ አንስተዋል።
 
መሰል ችግሮች እንዳይፈጠሩም እውቀት ያሥፈልጋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ለዚህ ደግሞ ቤተ መጻፍህት ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡
 
እውቀት ከድንቁርና ቀንበር ነጻ የሚያወጣ መንገድ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፥ታሪካችንን፣ ህዝባችንን እና ሀገራችንን ካላወቅን እንዲሁም የማድረግ አቅማችን ካላወቅን ከድንቁርና ልንላቀቅ አንችልም ነው ያሉት፡፡
 
በአፍሪካ ነጻ እና የራሷ ሆነ ፊደላት መፍጠር የቻለች ሀገር መድፈር ተገቢ አይደለም፤ ጠላቶቻችን ቀድመው እንዲያስቡ ቀድመን ከግጭት እና ከጦርነት በፊት ልካችንን እንዲያውቁ ማድረግ አለብንም ብለዋል።
 
መሰል መልካም አላማ ያላቸውን ተቋማትን መጀመር ብቻ ሳይሆን መጨረስ፣ መጨረስ ብቻ ሳይሆን መመረቅና በስርዓት መገልገል እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል።
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.