Fana: At a Speed of Life!

በምዕራብ ወለጋ ዞን 484 ተፋሰሶችን መሠረት ያደረገ የተፈጥሮ ሐብት ልማትና ጥበቃ ሥራ ተጀመረ

በምዕራብ ወለጋ ዞን 484 ተፋሰሶችን መሠረት ያደረገ የተፈጥሮ ሐብት ልማትና ጥበቃ ሥራ ተጀመረ

በምዕራብ ወለጋ ዞን 484 ተፋሰሶችን መሠረት ያደረገ የበጋ ወቅት የተፈጥሮ ሐብት ልማትና ጥበቃ ሥራ መጀመሩን የዞኑ እርሻና ተፈጥሮ ሐብት ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

በዞኑ ዛሬ የተጀመረው የተፈጥሮ ሐብት ልማትና ጥበቃ ሥራ ለመጪዎቹ ሁለት ወራት የሚካሄድ መሆኑም ተነግሯል፡፡

የጽህፈት ቤቱ የተፈጥሮ ሐብት ቡድን መሪ አቶ ፍቅሩ ብርሃኑ እንደገለጹት ÷ የተፈጥሮ ሐብት ልማትና ጥበቃ ሥራው በዞኑ 20 ወረዳዎች 300 ሄክታር መሬት ላይ ይካሄዳል።

የተፈጥሮ ሐብት ልማትና ጥበቃ ሥራው የማሳ ውስጥና የጋራ ላይ እርከን ጨምሮ የመሬት እርጥበትን ለመጠበቅና ለአካባቢ ጥበቃ የሚረዱ ሌሎች የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራዎች እንደሚከናወኑ ተናግረዋል።

በተጨማሪም 24 ሺህ 785 ሄክታር የተጎዳ መሬት ከሰውና ከእንስሳት ንክኪ የማካለል ስራ እንደሚካሄድ ጠቅሰዋል ።

በዘመቻ በሚካደው የልማት ስራ ከ281ሺህ በላይ አርሶ አደሮች እንደሚሳተፉ የቡድን መሪው መግለጻቸውን ኢዜአ አመላክቷል ።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.