Fana: At a Speed of Life!

የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን ሲያዘዋውሩ የነበሩ የሀረሪ ፖሊስ ኮሚሽን ሠራተኞች በቁጥጥር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን ሲያዘዋውሩ የነበሩ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ሠራተኞች በቁጥጥር ዋሉ።
የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ነስሪ ዘከሪያ እንደገለፁት፥ ግለሰቦቹ እኩይ አላማቸውን ለማሳካት የኮሚሽኑን የእሳትና ድንገተኛ አደጋ አምቡላንስ ሲጠቀሙ ነበር ብለዋል።
በዚሁ መሠረት በተደረገ ክትትል አምቡላንሷ በርካታ የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን ጭና ሲንትንቀሳቀስ በአዋሳኝ የኦሮሚያ ክልል አወዳይ ከተማ በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉ ነው የተገለፀው።
በወቅቱ የአምቡላንሷ አሽከርካሪ ለጥገና በሚል ተሸከርካሪዋን ከኮሚሽኑ ቅጥር ግቢ ይዟት መውጣቱም ተጠቁሟል።
የአምቡላንሱ አሽከርካሪ ለግዜው የተሰወረ ቢሆንም ግለሰቡን ለመያዝ እየተሰራ እንደሚገኝ ኮሚሽነሩ ጨምረው ገልፀዋል።
በህገወጥ ድርጊቱ የተሳተፉ የፖሊስ ኮሚሽኑ አባላትን የመለየት ስራ እየተሰራ ሲሆን፥ በወቅቱ ተገቢውን አመራር አልሰጡም በተባሉ አካላት ላይም እርምጃ ይወሰዳል ማለታቸውን ከክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
No photo description available.
0
People reached
60
Engagements
Distribution score
Boost post
51
9 Shares
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.