Fana: At a Speed of Life!

የአምባሳደር ዶክተር ካሳ ከበደ ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2014 ( ኤፍ ቢ ሲ) የአምባሳደር ዶክተር ካሳ ከበደ ስርዓተ ቀብር በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴደራል ተፈጸመ።

በቀብር ስነስርዓቱ ላይ አርቲስትና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ታማኝ በየነን ጨምሮ ሌሎች የቀድሞ የስራ ባልደረቦቹ፣ ወዳጅ ዘመዶቹ ተገኝተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣የኢትዮ ኩባ እና የህፃናት አምባ ልጆች፣ የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዚደንት ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም ተወካይ እና ሌሎች ተቋማትና ግለሰቦች የመታሰቢያ አበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል።

ከአምባሳደር ካሳ ከበደ ስርዓተ ቀብር አስቀድሞ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ስርዓትና ቀኖና መሰረት ፆለትና ፍትሃት መርሃ ግብር መካሄዱን ኢዜአ ዘግቧል።

አምባሳደር ዶክተር ካሣ ከበደ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ታህሳስ 16 ቀን2014 ዓ.ም በተወለዱ በ80 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.