Fana: At a Speed of Life!

በ4 ነጥብ 8 ሚሊየን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ በማህበራዊ ተግዳሮቶች ላይ የሚሰራ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣የካቲት 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአውሮፓ ህብረት የ4 ነጥብ 8 ሚሊየን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ ለ3 ዓመት የሚተገበር በማህበራዊ ተግዳሮቶች፣ በጤና እና በስርዓተ ጾታና እኩልነት ላይ የሚሰራ ፕሮጀክት በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ይፋ ተደርጓል፡፡
በፕሮጀክቱ ትውውቅ መድረኩ የተገኙት የክልሉ ምክትል ርዕስ መስተዳድር አቶ ጌታሁን አብዲሳ፥ ፕሮጀክቱ እንደ ሀገር ጤናማ ማህበረሰብ በመፍጠር ምርታማነት እንዲኖር በጤናው ዘርፍ የሚተገበሩ ስራዎችን በመደገፍ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለዋል፡፡
ፕሮጀክቱም በክልሉ በጤና ላይ እና በስርዓተ ጾታ ላይ የሚስተዋሉ ጉድለቶችን በሚቀርፍ መልኩ ተፈጻሚ እንዲሆን፥ የፕሮጀክቱ ተሳታፊ ባለድርሻ አካላት እና የክልሉ ሴክተሮች ከወቅታዊ ሁኔታው ጋር በማገናዘብ ለውጤታማ ስራ በኃላፊነት መንቀሳቀስ እንዳለባቸው ምክትል ርዕስ መስተዳድሩ አስገንዝበዋል፡፡
የክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ረጋሳ በበኩላቸው፥ ፕሮጀክቱ በአውሮፓ ህብረት የገንዘብ ድጋፍ በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ውል ሰጭነት በ4 ነጥብ 8 ሚሊየን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንዲገባ መደረጉ በመንግስት አቅም ሊሽፈኑ ያልቻሉ የጤና ፕሮግራሞችን በማዳረስ የክልሉን ጤና ሽፋን የሚያግዝ ነው ብለዋል፡፡
በተለይ ፕሮጀክቱ በሴቶች ላይና በታዳጊ ልጃገረዶች እንዲሁም ከ5 ዓመት በታች ያሉ ህጻናትን ጤና እና አመጋገብ ለማሻሻል በልዩ ትኩረት የሚሰራ ነው ብለዋል።
አቶ ፍቃዱ በፕሮጀክቱ በመታገዝም በክልሉ ሁሉን አቀፍ እድገት ለማስመዝገብ ባለድርሻ አካላት በጋራና በቅንጅት እንዲሰሩ መጠየቃቸውን ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.