Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል ከ300 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በቡና ተክል መሸፈኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በክልሉ የቡና ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ በከምባታ ጠምባሮ እና ወላይታ ዞን የሚገኙ ቡና አምራች አርሶ አደሮች የቡና ተክል እደሳ መርሃ ግብር እየተካሔደ ነው፡፡

በደቡብ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር እንደገለጹት፥ በቡና ልማት የተሰማሩ አርሶ አደሮች የራሳቸውን ገቢ ከማሳደግ ባለፈ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ለማጎልበት እየተሰራ ነው።

በክልሉ ከ300 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በቡና ተሸፍኗል ያሉት ኃላፊው፥ በዘርፉ የተሻለ ተሞክሮ ያላቸውን አርሶ አደሮች ወደ ሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ለማዳረስ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

በክልሉ 90 ሚሊየን የቡና ችግኞች ለመትከል መታቀዱን ጠቁመው፥ ከዚህ ውስጥ 40 ሚሊየን አዲስ ተከላ ይካሄዳል ነው ያሉት።

በክልሉ 3 ነጥብ 5 ሚሊየን አርሶ አደሮች በቡና ልማት ላይ እንደሚሳተፉም ተናግረዋል። 1 ነጥብ 9 ሚሊየን ቶን ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ እየተሰራ ነው ብለዋል።

የቡና ምርታማነት ማሳደግ እና ቡና ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ የሚያበረክተውን ሚና ግንዛቤ በመፍጠር እየተሰራ ነው ሲሉም አብራርተዋል።

የቡና ጥራት ማሳደግ እንዲሁም በዘርፉ የሚያጋጥመውን ህገወጥነት ለመከላከል በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም አረጋግጠዋል።

በመርሃ ግብሩ በቡና ልማት የተሻለ ልምድ ያላቸውን አርሶ አደሮች ማሳ ጉብኝት እና ያረጁ ቡናዎች ጉንደላ ተከናውነዋል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.