Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ፑቲን የሩሲያ የኑክሌር መከላከያ ሀይል በተጠንቀቅ እንዲቆም አዘዙ

አዲስ አበባ፣የካቲት 20፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የሀገሪቱ የኑክሌር መከላከያ ኃይል በተጠንቀቅ እንዲቆም አዘዙ።
ፕሬዚዳንቱ ትዕዛዙን የሰጡት ከሀገሪቱ የመከላከያ ሚኒስትር ሰርጌይ ሾይጉ እና ከካቢኔ ኃላፊ ቫለሪ ገራሲሞቭ ጋር ውይይት ካደረጉ በኋላ መሆኑ ነው የተገለፀው፡፡
“የምዕራባውያን አገራት በአገራችን ላይ ተገቢ ያልሆነ ማዕቀብ እየጣሉ ነው፣ የኔቶ ሀገራት ከፍተኛ ባለስልጣናትም ጠብ ጫሪ መግለጫዎችን እየሰጡ ነው፣ ለዚህም የኑክሌር መከላከያችን ዝግጁ መሆን አለበት ብለዋል” ፕሬዚዳንቱ።
የሩሲያ ኑክሌር ኃይል ለመከላከልና ለማጥቃት የሚውሉ የኑክሌርና ሌሎች መሳሪያዎችን የታጠቀ መሆኑን አር ቲ በዘገባው አመላክቷል፡፡

በሚኪያስ አየለ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.