Fana: At a Speed of Life!

ሩስያና ዩክሬን ሁለተኛ ዙር ውይይታቸውን ዛሬ እንደሚያካሂዱ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩስያና ዩክሬን የጀመሩትን ሁለተኛ ዙር የሰላም ውይይት ዛሬ እንደሚያካሂዱ የሩስያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰረጌ ላቭሮቭ አስታወቁ።
 
የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪም ሁለተኛው ዙር የሁለቱ አገራት የልዑካን ቡድኖች ውይይት ዛሬ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
 
በሁለቱ አገሮች ተወካዮች አማካይነት የሚካሄደው የዛሬው የሰላም ውይይት በቤላሩስ – ፖላንድ ደንበር አካባቢ እንደሚሆን ተጠቁሟል።
በሁለቱ አገሮች በኩል በውይይቱ ላይ የሚሳተፉት የልዑካን ቡድኖች በመጀመሪያው ዙር የተሳተፉት ልዑካን እንደሚሆኑ ሲጂቲኤን ዘግቧል።
 
የመጀመሪያው ዙር ውይይታቸው ከተነሱት ጉዳዮች መካከል፥ የተኩስ አቁም ስምምነትና ጥላቻን ስለማስወገድ፥ የሩስያ ወታደሮች ከዩክሬን የመውጣትና ሰላማዊ ድርድር የማካሄድ አጀንዳዎች የሚጠቀሱ ናቸው።
 
የሁለቱ አገራት የመጀመሪያው ዙር የሰላም ውይይት በቤላሩስ ደንበር አካባቢ ባለፈው ሰኞ መካሄዱ ይታወሳል።
 
በሩስያና ዩክሬን መካከል እየተካሄደ ያለው ጦርነት ከተቀሰቀስ ዛሬ 8ኛ ቀኑን ይዟል፡፡
 
በሌላ በኩል ሩስያና ቤላሩስ በዓለም አቀፉ የፓራኦሊምፒክ ውድድር እንዳይካፈሉ መታገዳቸው ተዘግቧል።
 
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.