ጉዳያቸውን በህግ ሲከታተሉ የነበሩ 60 ዜጎች ክስ ተቋረጠ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 16 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት በተለያየ ምክንያት ጉዳያቸውን በህግ ሲከታተሉ ለነበሩ 60 ዜጎች ክስ እንዲቋረጥ አደረገ።
የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ሃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ለኢቢሲ እንደተናገሩት፥ መንግስት የ60 ዜጎች ክስ ተቋርጦ ምህረት እንዲደረግ ወስኗል።
አያይዘውም የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋትና መንግስትም ሆነ ታራሚዎች በጉዳዩ ላይ ትምህርት የወሰዱበት በመሆኑ ምህረት መደረጉን አስረድተዋል።
ከዚህ ባለፈም መንግስት የዜጎችን ጥያቄ በማድመጥና ማህበራዊውን ሁኔታ በማየት መወሰኑን ተናግረዋል።
በክስ መቋረጡ ዝርዝር ሁኔታ እና አፈጻጸም ላይም ጠቅላይ አቃቤ ህግ መግለጫ እንደሚሰጥ ጠቅሰዋል።
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision