Fana: At a Speed of Life!

በሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንድ እስከ ሶስት በመውጣት ድል ተቀዳጁ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤልግሬድ በ18ኛው የዓለም የቤት ውስጥ የሩጫ ውድድር ምሽት 4:35 ላይ በሴቶች ምድብ የተደረገው የ1 ሺህ 500 ሜትር ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንድ እስከ ሶስት በመውጣት ድል ተቀዳጅተዋል።
በ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች የፍጻሜ ውድድር አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ 3 ደቂቃ ከ57 ሰከንድ ከ19 ማይክሮ ሰከንድ በማጠናቀቅ በርቀቱ የሻምፒዮናውን ክብረ ወሰን በመስበር ጭምር አሸንፋለች።
አትሌት አክሱማዊት አምባዬ 4 ደቂቃ ከ2 ሰከንድ ከ29 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ሁለተኛ ስትወጣ፥ አትሌት ሂሩት መሸሻ 4 ደቂቃ ከ3 ሰከንድ ከ39 ሰከንድ በመግባት ሶስተኛ ደረጃን ይዛለች።
ኢትዮጵያ በ3000 ሜትር ሴቶች በአትሌት ለምለም ኃይሉ አማካኝነት የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ ያገኘች ሲሆን÷ አትሌት እጅጋየሁ ታዬ ሶስተኛ በመውጣት የነሐስ ሜዳሊያ ማግኘቷ ይታወሳል፡፡
ኢትዮጵያ ሁለት ወርቅ፣ አንድ ብር እና ሁለት ነሀስ በድምሩ አምስት ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ የሻምፒዮናውን የሜዳሊያ ሰንጠረዥ በአንደኝነት እየመራች ነው።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.