Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ የወንዶች የቮሊቦል ጥሎ ማለፍ ውድድር መጋቢት 15 ይጀመራል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2014 ዓ.ም የኢትዮጵያ የወንዶች የቮሊቦል ጥሎ ማለፍ ውድድር መጋቢት 15 ቀን 2014 ዓ.ም እንደሚጀመር የኢትዮጵያ ቮሊቦል ፌዴሬሽን አስታወቀ።
በአዲስ አበባ ትንሿ ስታዲየም በሚካሄደው ውድድር ወላይታ ዲቻ፣ ሙገር ሲሚንቶ፣ መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ፣ ብሔራዊ አልኮል፣ አዲስ አበባ ፖሊስ፣ መከላከያ እና ባህርዳር ከተማ ይሳተፋሉ።
የጥሎ ማለፍ ውድድሩ ዓላማ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦችን የውድድር አማራጭ ማስፋትና በፈረንጆቹ 2023 የአፍሪካ የወንዶች ክለቦች የቮሊቦል ሻምፒዮና ኢትዮጵያን የሚወክል ክለብ ለመምረጥ መሆኑን የፌዴሬሽኑ የውድድር ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ብሩህ ተክለማርያም ለኢዜአ ገልጸዋል።
የክለቦች የጥሎ ማለፍ ውድድር ለመጨረሻ ጊዜ የተካሄደው በ2011 ዓ.ም በጎንደር ከተማ መሆኑን አስታውሰው÷ በኮቪድ-19 ወረርሽኝና በወቅታዊ ሁኔታዎች ምክንያት ውድድሩን ማካሄድ እንዳልተቻለ ተናግረዋል።
የስፖርት ቤተሰቡ በትንሿ ስታዲየም በመገኘት ውድድሩን እንዲከታተል አቶ ብሩህ ጥሪ አቅርበው÷ የኢትዮጵያ የወንዶች የቮሊቦል ጥሎ ማለፍ ውድድር እስከ መጋቢት 22 ቀን 2014 ዓም እንደሚቆይም ነው የተናገሩት።
በተያያዘ ዜና የ2014 ዓ.ም የኢትዮጵያ የሴቶች ቮሊቦል ፕሪሚየር ሊግ ተስተካካይ ጨዋታዎች ከመጋቢት 14 እስከ 24 ቀን 2014 ዓ.ም በትንሿ ስታዲየም እንደሚካሄዱ ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.