Fana: At a Speed of Life!

51ኛው የአትሌቲክስ ሻምፒዮና የፊታችን መጋቢት 19 ጀምሮ በሃዋሳ ይካሄዳል

 
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 51ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከመጋቢት 19 እስከ 24 ቀን 2014 ዓ.ም በሲዳማ ክልል ሃዋሳ ከተማ እንደሚካሄድ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።
 
በሻምፒዮናው ላይ የክልሎች፣ የከተማ አስተዳደሮች፣ የክለቦችና በአትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከላት የሚገኙ አትሌቶች ይሳተፋሉ ተብሏል።
 
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ1963 ዓ.ም የተጀመረ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን÷የሻምፒዮናው 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ ውድድር በ2013 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም ተካሂዷል፡፡
 
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአትሌቲክስ ቡድን በሁለቱም ጾታዎች በአጠቃላይ 12 የወርቅ፣ 10 የብር እና 5 የነሐስ በድምሩ 27 ሜዳሊያዎችን በማግኘት የውድድሩ አጠቃላይ አሸናፊ መሆኑ የሚታወስ ነው።
 
በሻምፒዮናው መከላከያ የስፖርት ክለብና የኦሮሚያ ክልል ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃን ይዘው ማጠናቀቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
 
በ50ኛው የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ስምንት የሻምፒዮናው ክብረ ወሰኖች መሻሻላቸው ይታወሳል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.