Fana: At a Speed of Life!

የተመድ ዋና ፀሃፊ የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦትን ለማቀላጠፍ ግጭት ለማቆም መወሰኑን አደነቁ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦትን ለማቀላጠፍ ግጭት ለማቆም መወሰኑን አደነቁ።

ጉተሬዝ በቃል አቀባያቸው በኩል ባወጡት መግለጫ መንግስት የሰብዓዊ ዕርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች የሚላከውን አቅርቦት ማሳለጥ እንዲቻል ግጭት ማቆሙን በአወንታ እንደሚቀበሉት አስታውቀዋል።

ግጭት በአፋር፣ አማራ፣ ትግራይ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝና ኦሮሚያ ክልሎች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ለችግር መዳረጉን ያነሱት ዋና ፀሃፊው፥ የመንግስትን መልካም ውሳኔ ሁሉም ወገን ወደ መሬት እንዲያወርደው ነው ያሳሰቡት።

በብርቱ የሚያስፈልገውን የሰብዓዊ እርዳታን በእነዚህ በግጭት የተጎዱ አካባቢዎች ለማድረስ ሁሉም ወገን እንዲረባረብም ነው ጥሪ ያቀረቡት።

የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦትን ለማቀላጠፍ ግጭት ለማቆም መወሰኑን ከትናንት በስቲያ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.