Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ሸኔ ሲጠቀምባቸው የነበሩ የጦር መሣሪያዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን ኑኑ ቁምባ ወረዳ በተካሄደ የተቀናጀ ኦፕሬሽን አሸባሪው ሸኔ ሲጠቀምባቸው የነበሩ 606 የተለያየ ዓይነት የጦር መሣሪያዎች እና 1 ሺህ 56 ጥይቶች ተያዙ፡፡
የጦር መሣሪያዎችም ከህብረተሰቡ የተዘረፉ መሆናቸውን የወረዳው ልዩ ሃይል ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ጌታቸው ግርማ ገልጸዋል።
ከጦር መሣሪያዎቹ በተጨማሪ 800 ኩንታል የተለያዩ የእህል አይነቶችና ሸኔ የሚጠቀምባቸው የደንብ ልብሶች መያዛቸውን የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ነጋሽ አለማየሁ ተናግረዋል፡፡
መሳሪያዎች የተያዙትም ከተቀበሩበትና ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት በተካሄደ ኦፕሬሽን መሆኑን ከምሥራቅ ወለጋ ዞን ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.