በወርሃዊው የፊፋ የአገራት ደረጃ ዋልያዎቹ ሁለት ደረጃዎችን ቀነሱ
አዲስ አበባ፣መጋቢት 22፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በወርሃዊው የፊፋ የሀገራት ደረጃ ሰንጠረዥ ዋልያዎቹ ሁለት ደረጃዎችን ዝቅ ብለዋል፡፡
ዓለም አቀፉ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል (ፊፋ) በየወሩ የዓለም ሀገራትን የአግር ኳስ ደረጃ ይፋ አድርጓል፡፡
ለበርካታ ወራት በደረጃው አናት ላይ የነበረችው ቤልጂየም ደረጃዋን ለብራዚል በማስረከብ ወደ ሁለተኛ ደረጃ ዝቅ ብላለች፡፡
ፈረንሳይ ደግሞ 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡
ሴኔጋል፣ ሞሮኮ እና ናይጀሪያ ደግሞ ከዓለም 20፣ 24ኛ እና 30ኛ ደረጃን በመያዝ ከአፍሪካ ቀዳሚዎች ሆነዋል፡፡
በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በየካቲት ወር ከነበረበት 138ኛ ደረጃ በዚህ ወር ሁለት ደረጃዎችን በመቀነስ 140ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡
ብሄራዊ ቡድኑ ከአፍሪካ በ42ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!