Fana: At a Speed of Life!

ተቋማቱ የመንግስት አገልግሎት የክፍያ ስርዓትን ለማዘመን ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ማስተር ካርድ የመንግስት አገልግሎት የክፍያ ስርዓትን ለማዘመን ተስማምተዋል፡፡

ተቋማቱ የኦንላይን የክፍያ ስርዓትን ለማዘመን በጋራ ለመስራት የተስማሙ ሲሆን ፥ በስምምነቱ መሰረት የመንግስት አገልግሎትን በኦንላይን የሚያገኙ ዜጎች የ ኢ-ሰርቪስ ፖርታልን በመጠቀም የዲጂታል ክፍያዎችን እንዲፈፅሙ ያስችላል ተብሏል፡፡

ስምምነቱ የክፍያ ሥርዓትን በማዘመን እና በክፍያ ስርዓት ውስጥ አካታች ሥነ-ምህዳርን በመፍጠር መንግስት የያዘውን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እቅድ እንደሚደግፍም ተገልጿል፡፡

በመጀመሪያው ዙር የትግበራ ምዕራፍ የሲቪል ማኅበራት ድርጅት አባላት ይህንን የክፍያ መተግበሪያ አማራጭ በመጠቀም ፈቃድ ለማውጣትና ለማደስ በቅርቡ ክፍያ መፈፀም እንዲችሉ ይደረጋልም ነው የተባለው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር በለጠ ሞላ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት ዳላክ ይገዙ፣ ከማስተር ካርድ ኢንሸሪያ አሊ እና ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሲቪክ ማህበረሰብ ተቋም ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል ፋሲካው ሞላ በስምምነቱ ተገኝተዋል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር በለጠ ሞላ በመርሀ ግብሩ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር “የእኛ ጥረት ኢትዮጵያን ከጥሬ ገንዘብ ህትመትና ስርጭት ወጪ ማላቀቅ እንዲሁም የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂን ተግባራዊ ማድረግ ነው” ብለዋል፡፡

እንደ ማስተርካርድ አለም አቀፍ ከሆኑ ኩባንያዎች ጋር በመተባበር ፈጠራ የታከለባቸው የክፍያ አማራጭ መሰረት ልማቶችን መዘርጋት በዜጎች እና በመንግስት መካከል የዲጂታል ግንኙነትን ለመፍጠር ያግዛልም ብለዋል፡፡

በፈትያ አብደላ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.