Fana: At a Speed of Life!

የሉሲ -ድንቅነሽ ኢትዮጵያ ባሕላዊ ሙዚቃ ትርኢት ሊካሄድ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሉሲ -ድንቅነሽ ኢትዮጵያ የተሰኘ ባሕላዊ ሙዚቃ ትርኢት ሊካሄድ መሆኑን የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
 
በሚኒስቴሩ የኪነ ጥበብና ስነጥ በብ የፈጠራ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ነፊሳ አልማሂዲ÷ “ሉሲ – ድንቅነሽ ኢትዮጵያ” ሙዚቃዊ ትርኢት ዓላማው እንደ ስያሜው በድንቅ ባህላዊ ሙዚቃና ውዝዋዜ ታጅቦ በላቀ ጥበባዊ ፈጠራ ቅንብር ተሰናድቶ፣ የሕዝቦች አብሮነት አጉልቶ በማሳየት ወቅታዊና ዘርፈ ብዙ ሀገራዊ ችግሮች ማከም ነው ብለዋል።
 
ከዚህ ባለፈም ትርኢቱ የጥበብን አስተዋጽኦ ማላቅና የሚጠበቀውን አገራዊ ገጽታ ግንባታን እውን ለማድረግ ያለመ መሆኑን አስረድተዋል ፡፡
 
ሥራው የተጀመረው ከሶስት ዓመት በፊት መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሯ÷ አንጋፋ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችን በመያዝ የሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች የባህል መስተጋብራቸው የሚገለጽበት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
 
ጸሐፊ ተውኔት ደራሲና ገጣሚ አያልነህ ሙላቱ በበኩላቸው ÷ ኪነ ጥበብ ኃያል ስለሆነ ከዚህ በፊት ”ሕዝብ ለሕዝብ” በተባለ ርዕስ በ1970 ዎቹ በአገራችን ደርሶ በነበረው ድርቅ ውለታ ለዋሉ የዓለም ሕዝቦች ምሥጋና ለማቅረብና የኢትዮጵያና መልካም ገጽታ ለማስተዋወቅ ሙዚቃዊ ትርኢት የቀረበበት ተሞክሮ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡
 
የትርኢቱ መጠሪያ ርዕስ ሉሲ-ድንቅነሽ ኢትዮጵያ የተባለበት ምክንያት ሉሲ- ድንቅ የተባለችው በእኛ ብቻ ሳይሆን በመላው ዓለም ጭምር መሆኑን ያሳያል፤ የሰው ዘር መነሻ እንደመሆኗ መጠንም መፈጠሪያዋን አገር ኢትዮጵያን ድንቅ አሰኝታታለች ነው ያሉት፡፡
 
በመሆኑም የሉሲ መገኛ ኢትዮጵያን ብዝሃነቷን፣ የታመቀ ሃብቷን፣ ታሪካዊና ባህላዊ ገጽታዋን ኃያል ጉልበትና አቅም ባለው በኪነ ጥበብ አማካይነት ገልጾ ማሳየት ከምንጊዜውም በላይ ዛሬ አስፈላጊ በመሆኑ ይህንን ሥራ እውን ለማድረግ በኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ትከሻ ላይ ማረፍ ለውጤት ለማብቃት ተግተን እየሠራን ነው ማለታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.