Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና ኬንያ በውጭ አገር ሥራ ስምሪት ዘርፍ የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ተስማሙ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 11 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ኬንያ በውጭ አገር የሥራ ስምሪት ዘርፍ የተሻሉ በተባሉ ተሞክሮዎች ላይ የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ተስማምተዋል፡፡
 
በሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ሥራ ስምሪት እና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በኬንያ ናይሮቢ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት እያደረጉ ነው፡፡
 
በናይሮቢ ቆይታቸውም ከኬንያ አቻቸው ፒተር ኬቱም ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መምክራቸውን በኬንያ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
በውይይታቸውም በውጭ አገር የሥራ ስምሪት ዘርፍ አገራቱ ባሏቸው ውጤታማ እና የተሻሉ ተሞክሮዎች ላይ የጋራ ልምድ ልውውጥ ለማድረግ መስማማታቸው ተገልጿል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.