Fana: At a Speed of Life!

ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ፍላጎት አላት – የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ሪቼል ኦማሞ በኬኒያ ከኢትዮጵያ አምባሳደር መለስ ዓለም ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ኢትዮጵያና ኬንያ ረዥም ዘመናትን ያስቆጠረና በቅርብ ወዳጅነት ላይ የተመሰረተ ጉርብትናና ወዳጅነት እንዳላቸው በማውሳት ለአፍሪካ ቀንድ ተምሳሌትና አስፈላጊ እንደሆነ ገልፀዋል።

በቀጣይ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር በኬንያ በኩል ፍላጎት መኖሩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ አስረድተዋል፡፡

በተጨማሪም የኢትዮጵያ መንግስት በጦርነት የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ለመገንባት ለሚያደርገው ጥረት ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ ምክክር ለማካሄድ ለሚደረገው ውይይትም መንግስታቸው እንደሚደግፈው መናጋራቸውን በኬንያ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አምባሳደር መለስ ዓለም የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን መልዕክት ለሚኒስትሯ አድርሰው በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡

በሁለቱ አገራት መካከል ያለው ታሪካዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊ ግንኙነት ወደ ኢኮኖሚያዊ፣ ህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ማደጉን ጠቅሰው ፥ በተለይ በስፖርት እና ዲፕሎማሲ ላይ ዘርፍ ብዙ ስራዎች መሰራታቸውን አሁን የተጀመረው በጎ ጅማሮ መጎልበት እንዳለበት ገልፀዋል።

አምባሳደሩ በኬንያ ቆይታቸው የሁለቱ አገራት ግንኙነት እንዲሻሻል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን በመግለፅ ሚኒስትሯ አመስግነው ፥ ኬንያ ከሌላ አገር ጋር ባላት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አምባሳደሮች የሚሰጠውን ልዩ ‘የአንበሳ ዱካ’ (Nyayo Simba) የክብር ሽልማት አበርክተውላቸዋል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.