Fana: At a Speed of Life!

መንግስት ‘’የሩሲያ ኤምባሲ የውትድርና ምልመላ ቅጥር አውጥቷል’’ የሚል መሰረተ ቢስ ወሬን ኤምባሲው ውድቅ ማድረጉን አደነቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መንግስት በኢትዮጵያ የሚገኘው ‘’የሩሲያ ኤምባሲ የውትድርና ምልመላ ቅጥር አውጥቷል’’ የሚል መሰረተ ቢስ ወሬን ኤምባሲው ውድቅ ማድረጉን እንደሚያደንቅ አስታወቀ፡፡

ኤምባሲው ምንም አይነት የቅጥር ማመልከቻ እንደማይቀበል እና በፈረንጆቹ 1961 የቪየና የዲፕሎማቲክ ግንኙነት ስምምነትን እንደሚያከብር ገልጿል።

የኢትዮጵያ መንግስት ከኤምባሲው ጋር በመሰል አግባብ በሌላቸው የቅጥር ጉዳዮች ላይ ተስማምቶ ከተገኘ የቪየና የዲፕሎማሲ ግንኙነት ስምምነትን የሚጥስ ሲሆን ፥ ይህም የዲፕሎማቲክ ሚሲዮንን ተግባር እንደሚጻረር ይታወቃል።

ስምምነት ከመጣሱም ባሻገር የዲፕሎማቲክ ሚሲዮኖች የአገርን ህግና ደንብ አለማክበር እንደሆነም ነው የተመለከተው፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ኤምባሲው ለወሰደው ፈጣን እርምጃ ኤምባሲውን ማድነቁን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.