Fana: At a Speed of Life!

“ከኢድ እስከ ኢድ ወደ ሀገር ቤት” ጥሪን በመቀበል ከተለያዩ የዓለም አገራት እንግዶች እየገቡ ነው

አዲስ አበባ፣ሚያዝያ 14፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “ከኢድ እስከ ኢድ ወደ ሀገር ቤት” ጥሪን ተከትሎ ከተለያዩ የዓለም አገራት እንግዶች ወደ አገር ቤት እየገቡ መሆናቸው ተገለፀ፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ያቀረቡትን “ከኢድ እስከ ኢድ ወደ ሀገር ቤት” ጥሪ ተቀብለው የመጡ እንግዶች ለኢዜአ በሰጡት አስተያየት፤ በቀረበው ጥሪ መሰረት ኢድን በጋራ እያከበርን፣ የተቸገሩ ወገኖችን በመጠየቅና በማገዝ ጥሩ ቆይታ ልናደርግ መጥተናል ብለዋል፡፡

በተለይ በጦርነት ጉዳት በደረሰባቸው አካባቢዎች ተዘዋውሮ በመጎብኘት አቅማቸው የቻለውን ሁሉ ድጋፍ ለማድረግ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል፡፡

በመንግስት የተደረገው ጥሪ ወገኖችን ከማገዝ በተጨማሪ ቤተሰብን አግኝቶ ኢድን በጋራ ለማሳለፍም ልዩ አጋጣሚ መሆኑን ገልጸዋል።
ኢድን በጋራ ለማክበር የተገኙት የዲያስፖራ አባላት በቆይታቸው የተቸገሩ ወገኖችን በማገዝ ወደ መጡበት ሲመለሱ ደግሞ የአገራቸው አምባሳደር በመሆን የኢትዮጵያን እውነታ የሚያስረዱ መሆኑን ከኢድ እስከ ኢድ ብሔራዊ ኮሚቴ ጣምራ ሰብሳቢ ዑስታዝ አቡበክር አህመድ ገልጸዋል።

ለኢድ የሚመጡት በዓሉን አክብረው በአገራቸውም ኢንቨስት የማድረግ እድል እንዲያገኙ እየተመቻቸላቸው መሆኑን ተናግረዋል።

በ “ከኢድ እስከ ኢድ” ጥሪ የጎረቤት አገራት የእምነቱ ተከታዩች እና የሃይማኖት መሪዎች ጥሪ የተደረገላቸው መሆኑንም ዑስታዝ አቡበከር አህመድ አስታውሰዋል።

ኢትዮጵያ በእስልምና ታሪክ ትልቅ ድርሻ ያላትና ታሪካዊ አገር በመሆኗ ዓለም በቅጡ እንዲያውቃት የሁላችንም ጥረት ሊታከልበት ይገባል ሲሉ ዑስታዝ አቡበከር መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.