ኤች አር 6600 እና ኤስ 3199 ረቂቅ ህጎች እንዳይጸድቁ ሁሉም ኢትዮጵያውያን በጋራ መቆም እንዳለባቸው ምሁራን ጠየቁ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኤች አር 6600 እና ኤስ 3199 ረቂቅ ህጎች እንዳይጸድቁ ሁሉም ኢትዮጵያውያን በጋራ መቆም አለባቸው ሲሉ የፖለቲካ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁራን ተናገሩ፡፡
በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር ሴኔሳ ደምሴ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ ÷የፖለቲካ ልዩነቶች ቢኖሩም እንኳ የሀገርን ብሄራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ሁሉም ኢትዮጵያውያን በአንድነት መቆም አለባቸው ብለዋል።
በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ ጉዳዮች ተመራማሪ በቀለ ሀብታሙ ÷ረቂቅ ህጎቹ የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም ከመጉዳት ባሻገር ምስራቅ አፍሪካንም ይጎዳሉ ነው ያሉት፡፡
በመሆኑም ረቂቅ ህጎቹ እንዳይጸድቁ መተባበር እና አንድነት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
በህዝብ እና በመንግስት መካከል ጠንካራ ግንኙነት መፍጠር እና አንድ ሀሳብ መያዝ ሀገር ላይ የሚቃጣን አደጋ ለመመከት ያግዛል ብለዋል ምሁራኑ፡፡
ረቂቅ ህጎቹ እንዳይጸድቁ መንግስትም የዲፕሎማሲ ስራን አጠናክሮ መስራት እንዳለበት አመላክተዋል።
በአሜሪካ ኮንግረስ እና ሴኔት አባላት ኤች አር 6600 እና ኤስ 3199 የተሰኙ ረቂቅ ህጎችን በኢትዮጵያ ላይ ለማሳለፍ መቅረባቸው ይታወሳል፡፡
ይህን ተከትሎም ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በተደጋጋሚ ረቂቅ ህጎቹ እንዳይጸድቁ ተቃውሞ እያደረጉ ይገኛል።
ለጊዜው ረቂቅ ህጎች እንዲዘገዩ መደረጋቸው ይታወሳል።
በአልማዝ መኮንን
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!