አምባሳደር መለስ አለም በኬንያ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ሙዋይ ኪባኪ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኬንያ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን እና ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር መለስ አለም በኬንያ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ሙዋይ ኪባኪ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል፡፡
አምባሳደር መለስ ሀዘናቸውን የገለጹትበኬንያ ፓርላማ በሚገኘው የሙዋይ ኪባኪ የአስከሬን ሽኝት መርሐ ግብር ላይ በመገኘት ነው፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይ አምባሰደር መለስ÷ የኬንያ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ኪባኪ የላሙ ወደብ ፕሮጀክት መሰረት እንዲጣል ትልቅ ሚና መጫወታቸውን ገልጸዋል፡፡
አምባሳደር መለስ አክለውም÷ የኢትዮ-ኬንያ ሁለገብ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዲጠናከር እና በተለይም ሁለቱ ሀገራት የጋራ ኢኮኖሚያዊ መሠረተ ልማት ግንባታዎች እንዲከናወኑ ኪባኪ ትልቅ ሚና እንደነበራቸው አስታውሰዋል፡፡
የሙዋይ ኪባኪ አስከሬን በኬንያ ፓርላማ ሕንፃ ውስጥ ለሶስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን÷ በፈረንጆቹ ሚያዝያ 29 በኒያዮ ብሔራዊ ስታዲየም የአስከሬን ሽኝት መርሐ ግብር እንደሚካሄድ በኬንያ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!