Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮ ቴሌኮም “አሻም” እና “ቴሌ ገበያ” የተሰኙ አዳዲስ አገልግሎቶችን አስተዋወቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም አሻም እና ቴሌ ገበያ የተሰኙ አዳዲስ አገልግሎቶችን አስተዋወቀ፡፡
“አሻም” የተሰኘው አገልግሎት የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች አገልግሎት ሲያገኙ በሚሰበሰብላቸው ነጥብ መልሶ የሚከፍል አገልግሎት ሲሆን አገልግሎቱ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ መሆኑን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ ተናግረዋል።
“አሻም” ደንበኞች አየር ሰዓት ሲገዙ፣ በቴሌብር ሲገበያዩ እና የተለያዩ አገልግሎቶችን ሲጠቀሙ የሚያዝ ነጥብ ተመልሶ አገልግሎት እንዲገዙበት የሚያስችል መሆኑንም ነው የተናገሩት።
በተሰበሰበው ነጥብ ደንበኞች መልሰው የአየር ሰአት መግዛት ወይም ለወዳጅ ዘመድ ማስተላለፍ ይችላሉ ተብሏል፡፡
ሌላው በዚሁ ወቅት የተዋወቀው አገልግሎት “ቴሌ ገበያ” ሲሆን÷ ይህን አገልግሎት ደንበኞች ቴሌ ገበያ ethio telecom.et በመጠቀም በሽያጭ ማዕከላት የሚገኙ የሞባይል ቀፎዎችንና ታብሌቶችን በቴሌ ብር በመጠቀም የሚገበያዩበት አገልግሎት መሆኑ ተገልጿል።
በትዕግስት ብርሃኔ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.