ሩሲያ በዩክሬን ዛፖሮዢ ከተማ የሚገኝ የጦር መሳሪያ ማከማቻን ማውደሟን አስታወቀች
አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 19 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ ከምዕራባውያን ሀገራት ለዩክሬን የተላኩ የጦር መሳሪያዎች የሚገኙበትን የጦር መሳሪያ ማከማቻ ማውደሟን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ከአሜሪካ እና ከምዕራባውያን ሀገራት ወደ ኪየቭ የተላኩ ትላልቅ የጦር መሣሪያ እና ጥይቶች የተከማቹበት በደቡብ ምስራቅ ዩክሬን የሚገኝ የጦር መሳሪያ ማከማቻ ትናንት ምሽት በሩስያ ሚሳኤል ተመቶ መውደሙን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኮናሼንኮቭ ተናግረዋል፡፡
የሩሲያ የጦር አውሮፕላኖች በአንድ ሌሊት 59 የዩክሬን ወታደራዊ ኢላማዎችን መምታታቸውንም ቃል አቀባዩ ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም በዚሁ ምሽት የሩሲያ ሃይሎች 573 ድብደባዎችን በኪየቭ ሃይሎች ላይ ሲፈጽሙ፥ 18 ሰው አልባ አውሮፕላኖችም በጥይት ተመተው ከጥቅም ውጭ ሆነዋል ነው የተባለው፡፡
ሞስኮ ባለፈው ሰኞ ከምዕራባውያን እና ከአሜሪካ ለኪየቭ የተበረከቱ ወታደራዊ መሳሪያዎችን ለዩክሬን ሃይሎች ለማድረስ ያገለግሉ ነበር ያለቻቸውን በምዕራብ ዩክሬን የሚገኙ ስድስት የባቡር ሀዲዶች ማውደሟንም አር ቲ ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!