Fana: At a Speed of Life!

የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ለአፋር ክልል ከ54 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው የአፋር ክልል የዘርፉ ተቋማት ከ54 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አደረገ፡፡
ድጋፉን የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ወይዘ ሙፈሪሃት ካሚል ለአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አወል አርባ ሰመራ በመገኘት አስረክበዋል፡፡
አሸባሪው ትህነግ በአማራ እና አፋር ክልሎች በፈፀመው ወረራ እና በተካሄደው ጦርነት ምክንያት ከተከሰተው ሰብዓዊ ቀውስ ባሻገር በርካታ መሰረተ-ልማቶችና ተቋማት ሲወድሙ ቀላል የማይባሉት መዘረፋቸው ይታወሳል፡፡
በጦርነቱ ከፍተኛ ውድመትና ዘረፋ ካስተናገዱ ተቋማት መካከልም የቴክኒክ እና ሙያ ኮሌጆች፣ የጥቃቅን፣ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች እንዲሁም የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫዎች ጣቢያዎች ይገኙበታል፡፡
በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትም በአራት ዞኖች ውስጥ የሚገኙ ሦስት የቴክኒክና ሙያ ተቋማት እና 119 የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ከፍተኛ የሆነ ዝርፊያና ውድመት ደርሶባቸዋል፡፡
ሚኒስቴሩ ጉዳት የደረሰባቸውን ተቋማት ሥራ ለማስጀመር በዘርፉ የክልል ቢሮዎችን፣ ኮሌጆችን፣ና ተጠሪ ተቋማትን እና አጋር አካላትን በማስተባበር እና ትስስር በመፍጠር 1 ሺህ 812 ማሽነሪዎችን፣ 24 ሺህ 39 የእጅ መሳሪያዎችን፣ 4 ሺህ 296 ቁሳቁስ፣ 8 ሺህ 580 የስልጠና ግብዓቶችን፣ 6 ሺህ 157 የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎችን ማሰባሰብ ተችሏል፡፡
ይህም ለስልጠና ማስጀመሪያ እንዲሆን በሚል የተሰባሰበው ድጋፍ በገንዘብ ሲተመን 223 ሚሊየን 482 ሺህ ብር በላይ ይገመታል፡፡
ከዚህ ውስጥ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ከ54 ሚሊየን ብር በላይ የተገመተ 307 ማሽነሪዎች፣ 1 ሺህ 79 የእጅ መሳሪያዎች፣ 3 ሺህ 828 የተለያዩ ቁሳቁስና የሥልጠና ግብዓቶች በአይነት እና በገንዘብ ማበርከቱን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.