የፊቼ ጫምባላላ በዓል የዛሬው መርሐ ግብር በሰላም መጠናቀቁን የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አስታወቀ
አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 21 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ ፊቼ ጫምባላላ በዓል የዛሬው መርሐ ግብር
በሰላም መጠናቀቁን የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አስታወቀ።
በሰላም መጠናቀቁን የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አስታወቀ።
የቢሮው ሀላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ከፍተኛ ህዝብ የተገኘበት በዓል ያለ አንዳች ኮሽታና ችግር በሰላም መጠናቀቁን ተናግረዋል።
በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላደረጉ የፀጥታ አካላትና መላው የክልሉ ህዝብ ምስጋና አቅርበዋል።
በዓሉም ለሚቀጥሉት 15 ቀናቶች በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ይከበራል ተብሏል።
በብርሃኑ በጋሻው